ኡማ ፕሮሞሽን እና ኢቨንትስ የአብስራን ሆቴል ምርቃት በብቃት በመምራት አጠናቋል።

በልማታዊ ባለሀብት አቶ አዳነ ሹመቴ የተገነባው የአብስራ ሆቴል በደማቅ ፕሮግራም ተመረቀ።

በዎላይታ ሶዶ ከተማ የሆስፒታል ፣ ባንክ እና ሆቴል አገልግሎት የሚሰጠው ህንጻው የከተማውን የንግድ ስራ እንደሚያቀላጥፍ ተገልጿል።

ኡማ ፕሮሞሽን እና ኢቨንትስ ይህንን ደማቅ የምረቃ ስነስርዓት ከመድረክ ዝግጅት እስከ ፕሮግራም መምራት ድረስ በባለሞያዎች ታግዞ አሰናድቶታል።

“ባለሀብቱ አቶ አዳነ ሹመቴ ከአንድ መቶ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የገነቡት ህንፃ ለዎላይታ ሶዶ ከተማ ተጨማሪ የልማት አቅም መፍጠሩን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ አስታውቀዋል።

አቶ አክሊሉ አክለውም በዛሬው እለት የተመረቀው ህንፃ የልማት መነሳሳትን የፈጠረ ነው ሲሉም ተናግረዋል ።

ከወቅታዊ የልማት ሁኔታ ልዩ ትርጉም የሚሰጠው ስለመሆኑ ያብራሩት አቶ አክሊሉ የጤና ቱሪዝም እንቅስቃሴ አንፃርም ተጠቃሹ ግሬስ ሆስፒታል ለዎላይታ እና አጎራባች ህዝባች በዚሁ ህንፃ ላይ አዲስ ትሩፋት ይዞ መጥቷል ብለዋል።

የትኛውም ኢትዮጵያዊ ዘር እና ብሄር ሳይለይ በአቃፊነት እና አብሮነት ለለውጥ በመስራት የሚታወቀው የዎላይታ ህዝብ የልማት ብስራት ሆኖ እንደሚቀጥል የዞኑ አስተዳደሪ አቶ አክሊሉ አስረድተዋል።

የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ አቶ ተመስገን አለማየሁ
አሁንም በከተማችን ተስፋ ሰጪ ኢንቨስትመንቶች አሉ ሲሉ ተናግረዋል።

በአምራች ኢንዱስትሪ እና በተለያዩ ዘርፎች የሚያለሙ ባለሀብቶችን ፈጥነው እንዲሰሩ እናበረታታለን ሲሉም ክቡር ከንቲባው ገልፀዋል።

አቶ ተመስገን ዛሬ የተመረቀው የአብስራ ሆቴል ምቹ የማረፊያ አማራጭ ከመሆኑም ባሻገር በፈጣን ግንባታ መጠናቀቁ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

በርካታ የስራ እድል የፈጠረው የአብስራ ሆቴል
የከተማውን ኢኮኖሚ እና ገፅታ በጉልህ እንደቀየረው ከንቲባው አቶ ተመስገን ገልፀዋል።

አልሚው ባለሀብት አቶ አዳነ ሹመቴ ባስተላለፉት መልእክት ለህዝብ እና ለዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ምስጋና አቅርበዋል።

ዎላይታ የሁሉም ብሄሮች መኖሪያ እና ልዩ ሰላማዊ ስፍራ መሆኗን ከ1986 ጀምሮ ኖሬ አይቻለሁ ሲሉ ስራ ወዳዱ ባለፀጋ አቶ አዳነ ተናግረዋል።

አቶ አዳነ የከተማውን ገቢ እና ገፅታ ግንባታ እያሻሻለ ከሚገኘውን የአብስራ ሆቴል በተጨማሪ ሌሎችም ኢንቨስትመንቶችን ለማካሄድ እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።

ለስራው ስኬታማነት የገንዘብ የእውቀት እና ሞራል ድጋፍ ያደረጉትን ሁሉም ባለድርሻዎች የአቶ አዳነ ባለቤት ወይዘሮ አለምነሽ አባይነህ አመስግነዋል።

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ አቶ አዳነ እና ቤተሰቦቻቸው
ለኢንቨስትመንት ያላቸውን ተነሳሽነት እና ፈጣን ልማትን የመተግበር አቅምን እውቅና እና ልዩ ልዩ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

በእለቱ የተገኙ የስራ ባልደረቦቻቸው እና ህብረተሰቡ አቶ አዳነ  አስተዋይ አባት እና አቅመ ደካሞችን የሚደግፉ መሆናቸውን መናገራቸውን የዎላይታ ሶዶ ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች  ፅህፈት ቤት ዘግቧል።”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top