የልቦና ውቅር(Mindset)


ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በውቅረ ልቦና /ማይንድሴት/ ላይ ትኩረት ያደረገ የማነቃቂያ ስልጠና ተሰጥቷል።

ስልጠናው መቀመጫውን ደቡብ ኮርያ ካደረገው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ህብረት /International Youth Fellowship/ከተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል።

በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ እንደገለጹት፡ በልቦና ውቅር (ማይንድሴት) ላይ ግንዛቤን መስጠት ለጠንካራ አመለካከት እና ስብዕና ግንባታ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።

“ከፍ ያለ ዓላማ አንግበን ውጤት ለማስመዝገብ መስራት መቻል አለብን” ያሉት ፕሮፌሰር ታከለ፤ ትጉህ፣ ታታሪ እና ውጤታማ አገልጋይ እንድንሆን ስልጠናው አጋዥ በመሆኑ ትኩረት ሰጥተን እንከታተል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ወጣቶች ህብረት (International Youth Fellowship) አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር ናም ፒል ህዩን ለተማሪዎች ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን፤ ውስን ሃብቶች ላይ ትኩረት በመስጠትና በመቀናጀት ደቡብ ኮሪያ ከነበረችበት ድህነት ተላቅቃ አሁን ወዳለችበት ብልፅግና እንዴት እንደደረሰች ገለጻ ሰጥተዋል፡፡

ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው ሊኖራቸው ስለሚገባ ዲሲፒሊን፤ አሉታዊ እና ጠቃሚ ያልሆነ አስተሳሰብን በመለወጥ አዎንታዊ አመለካከትን ስለማዳበር እንዲሁም በሀገር ጉዳይ ገንቢ አስተዋጽኦን ከማበርከት አንጻር ኃላፊነታቸውን ለመወጣት መነሳሳት በሚፈጥሩ ርዕሰ ጉዳዮች ስልጠናው ተሰጥቷል።

ሀገርን ብሎም ዓለምን ለማልማት የሳይንሳዊ እውቀት፣ ቆራጥነት፣ ተነሳሽነት እና የዳበረ ቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊ መሆኑን ዶክተር ናም ፒል ህዩን ለተማሪዎች ተናግረው፤ በአጠቃላይ የማይንድሴት/የልቦና ውቅር ስልጠና ሁሉን አቃፊ፣ አገናኝ፣ አነቃቂ፣ ለፈጣን እና ዘላቂ ለውጥ መሰረት መሆኑንም ጠቁመዋል።

“ጥልቅ የማሰብ ችሎታን መጨመር፣ ጠንካራ አስተሳሰብን ማዳበር እና በመለዋወጥ የአንድነት ኃይልን መገንባት” ለውቅረ ልቦና/ማይንድሴት መሰረት መሆኑ በስልጠናው ተብራርቷል።

የስልጠናው ተሳታፊ ተማሪዎች በውቅረ ልቦና/ማይንድሴት ላይ ትኩረት ባደረገው የማነቃቂያ ስልጠና የተካተቱ ርዕሰ ጉዳዮች ጉልህ አዎንታዊ አስተሳሰብን ለማዳበር የሚረዱ፣ በቀጣይ የሕይወት ጉዞ ስርነቀል አዎንታዊ ለውጥ እንድናመጣ የሚያስችል እና ኃላፊነትን በአግባቡ ለመወጣት ግንዛቤን የሚፈጥር ነው ሲሉ ተናግረዋል።

#ኡማ_ኘሮሞሽን_እና_ኢቨንትስ ይህን መደረክ እንደ ተጠበቀው በብቃት በመምራት ለመድረኩ ስኬት የራሱን ድርሻ ተውቷል፡፡

#ኡማ_ኘሮሞሽን_እና_ኢቨንትስ

⬧︎ለደማቅ የመድረክ መምራትና ማማከር ሥራ

⬧︎ለሬድዮ እና ቴሌቪዝዥን ማስታወቂያዎች

⬧︎ለዶክመንታሪ ፊልም ዝግጅት

⬧︎ለሮድሾውሥራ

አጠቃላይ የሚዲያ ማማከር አገልግሎት

ፍላጎት ሲኖርዎ በ0911764351/0920464748 ይደውሉ አልያም

ወላይታ ሶዶ 21 ማዞሪያ ጥላሁን ሞል ቢሮ ቁጥር 218 በአካል ብቅ ይበሉ::

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top